በቤንሻንጉል ጉሙዝ 2 ሚሊዮን ችግኝ ለተከላ ተዘጋጅቷል

90
አሶሳ ኢዜአ ሐምሌ 16/2011 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሀምሌ 22 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔደውን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ 2 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ ። የቢሮ ኃላፊው አቶ ሙሳ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት በክልሉ ከዚህ ቀደም ችግኝ ባለቤትነት አይተከልም ነበር። ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም  በሃገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል  በሚደምቀው የአረንጓዴ አሻራ ቀን እቅድ በክልሉም 2 ሚሊዮን ችግኞችን ለማልማት ዝግጅት ተደርጓል ። "እስካሁንም በአምስት ወረዳዎች 500 ሺህ ጉድጓዶች ተዘጋጅተዋል" ያሉት ኃላፊው በቀሪ ወረዳዎችም በጥቂት ቀናት ውስጥ በቂ ጉድጓዶች እንደሚሰናዳ አመልክተዋል፡፡ በክልሉ ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞች በመንከባከብ ረገድ ድክመቶች መኖራቸውን ገልጸው “በዚህ ዓመት ባለቤት የሌለው ችግኝ አይኖርም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በተለይም እያንዳንዱ ተቋም ለሚተክለው ችግኝ ዘላቂ እንክብካቤ እንዲያደርግ ከቢሮው ጋር ተፈራርሞ ቦታ እንደሚረከብ አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸው "ችግኞቹን በተሻለ የሚያለሙ የሚበረታቱበትና ተገቢው እንክብካቤ ያላደረጉ የሚጠየቁበት አሰራር ተግባራዊ ይሆናል" ብለዋል ። የአሶሳከተማነዋሪውአቶአህመድአብዱላሂእንደተናገሩትየሀገርአቀፍችግኝተከላእቅድምክንያትበማድረግእስካሁንአስር  ችግኞችተክለውእየተንከባከቡነው፡፡ በዘላቂነት እንደሚያጸድቁት ገልጸው በጋራ በሚተከሉ ፕሮግራሞች በመሳተፍ አሻራቸውን ለማኖር መዘጋጀታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ በክልሉ በአጠቃላይ በተያዘው የክረምት ወቅት በ57 ችግኝ ጣቢያዎችና በአርሶ አደሮች 50 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል። 38 ሚሊዮን ችግኞች ለተከላ የተሰራጩ ሲሆን እስካሁንም እስከ አሁን ድረስ 6 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ከክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም