የሶማሊያ መከላከያ ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገደለ

149
ኢዜአ ሃምሌ14/2011 ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች የተገደሉት በደቡባዊ ሶማሊያአርብ ምሽት በተካሄደ ኦፕሬሽን ሲሆን የሶማሊያ ሃይል በአውድኒል ከተማ ባካሄደው ስምሪት ነው ተብሏል፡፡ የከተማዋ አስተዳዳሪ ኢብራሂም መሃመድ ኑር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የሶማሊያ ሃይል እርምጃውን የወሰደው የከተማዋ ነዋሪዎች “ጽንፈኛው አልሻባብ አስገዳጅ ግብር እንድንከፍል አድርጎናል” በሚል በሰጡት ጥቆማ ነው ፡፡
“በተካሄደው ኦፕሬሽን ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ አንዱ ከነህይወቱ በቁጥጥር ስር ውሏል፤የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችንም መያዝ ተችሏል”ያሉት አስተዳዳሪው የተያዘው ታጣቂም በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪ ለዥንዋ በስልክ በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው በከተማዋ በሶማሊያ መንግስት ሃይልና በበአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል አርብ ምሽቱን የተኩስ ልውውጥ እነደነበር ተናግሯል፡፡ የሶማሊያ ሃይል አሁን ከወሰደው እርምጃ በፊት በዋንሎዌይን ከተማ በሎወር ሸበሌ ክልል 15 የአልሻባብ ታጣቂዎቸን ግድሏል፡፡ የሶማሊያ ሃይል በማእከላዊና በደቡብ ሶማሊያ መጠነ ሰፊ ኦፕሬሽኖች በማካሄድ የአልሻባብ ጽንፈኞች አካባቢውን እንዲለቁ እየሰራ ነው፡፡ ምንጭ፡-ሲጂቲን አፍሪካ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም