አልጀሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች

87
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 13/2011 በ32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋልን የገጠመችው አልጄሪያ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች፡፡ አልጄሪያ ዋንጫውን ያነሳቸው በጨዋታው  ባዳግዳድ ቡኒጃ የተሰጠውን ቅጣት ምጥ ከመረብ በማስቆጠሩ ነው፡፡ ሴኔጋል በተደጋጋሚ ወደጎል በመቅረብ የተለያዩ የግብ ሙከራዎች ብታደርግም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ ጨዋታው በካይሮ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተካሄደበት ወቅት በርካታ የአልጄሪ ደጋፊዎች ተገኝተው ነበር፡፤ አልጄሪ በ1990 ካገኘችው ዋንጫ ጋር ይህ ሁለተኛዋ ሆኗል፡፡ በዚህም ሳቢያ የአልጀርስ ጎዳናዎች ምሽቱን ከፍተኛ ፍንደቃ ታይቶባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም