አሜሪካ የጦር መርከቤን ተጠግቷል ያለችውን የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏን አስታወቀች

129
ኢዜአ ሀምሌ 12/2011የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተናገሩት የአሜሪካ ባህር ሃይል የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን በስትሬት ኦርሙዝ መትቶ ጥሏል ብለዋል፡፡ ኢራን ግን ምንም አይነት ሰው አልባ አውሮፕላን እንዳልተመታባት ተናግራች፡፡
ይህን ተከትሎ በሁለቱ አገሮች የተፈጠረው ውጥረት እየተባባሰና አገራቱን ወደ ጦርነት እንዳያስገባቸው ስጋቶች ጨምረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ አሜሪካ የጦር መርከብ መቅረቡን ተከትሎ የመከላከያ እርምጃ ባህር ሃይሉ ወስዷል ብለዋል፡፡ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ወደ አሜሪካ የጦር መርከብ በጣም የተጠጋ መሆኑን ተከትሎ ይህም ለመርከቡ አደጋ የሚፈጥር በመሆኑ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ ቴሄራን ግን ሰው አልባ አውሮፕላን ስለመመታቱ ምንም መረጃ አልደረሰኝም ብላለች፡፡ በሰኔ ወር ላይ ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏ ይታወሳል፡፡ አሜሪካ ኢራንን ከግንቦት ወር ጀምሮ በአለም የመርከብ መንቀሳቀሻ ቦታ ላይ የሚንቀሳቀሱ ነዳጅ ጫኝ ታንከሮችን እያጠቃች መሆኑን እየወቀሰች ትገኛለች፡፡ ኢራን ግን “ህገ ወጥ ነዳጅ ጫኞችን ነው እየተከላከልኩ ያለሁት” ስትል የአሜሪካን ወቀሳ አጣጥለዋለች፡፡ በአሜሪካና በኢራን እየተፈጠረ ያለው የሰሞኑ ክስተት በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት እንዳያስነሳ ተፈርቷል፡፡ ምንጭ፡- ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም