በኮንጎ የተከሰተው ኢቦላ ዓለም አቀፋዊ የማህበረሰብ ጤና ስጋት መሆኑ ታወጀ

ሐምሌ 11/2011 በኮንጎ የተከሰተው ኢቦላ ዓለም አቀፋዊ የህብረተሰብ የጤና ስጋት መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በይፋ አውጇል።
ውሳኔው የበለጸጉ ሃገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ በር ከፋች ነው ተብሏል።
በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ከነሃሴ 2018 ወዲህ ከ1 ሺህ 600 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
በዚህ ሳምንት በሀገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በሚኖሩባት ጎማ ከተማ ውስጥ ኢቦላ እንደ አዲስ ተከስቷል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጄኔቫ ላይ የኢቦላን ዓለም አቀፋዊ ስጋትነት ሲያውጁ ዓለም የአደጋውን አሳሳቢነት ማወቅ አለበት ብለዋል።
በኮንጎ የተከሰተው ኢቦላ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 500 የደረሰ ሲሆን ከታማሚዎች ውስጥ ሁለት ሦስተኛው ሞተዋል።
በየቀኑ 12 ሰዎች በበሽታው ተጠቂ መሆናቸው ሪፖርት እንደሚደረግም መረጃዎች እንደሚያሳዩ የዘገበው ቢቢሲ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም