በቶኬ ኩታዬ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ 20 ኩንታል ቡና ተያዘ

60
አምቦ( ኢዜአ)ሐምሌ 8 / 2011 በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ በሕገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ተጭኖ ይጓጓዝ የነበረ 20 ኩንታል ቡና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። ቡናው  ጉደር ኬላ ፍተሻ ዜሮ ዜሮ የተባለ አካባቢ  ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 –54459 አዲስ አበባ በሆነ አይሱዙ  ተሽከርካሪ ላይ ተሸሸጎ እንደተጫነ ሊያዝ ችሏል። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አገሪ ደፋሊ እንዳሉት ቡናው የተሸሸገው 50 ኩንታል ገብስ ከላይ ጭኖ ከጅባት ወረዳ ወደ አዲስ አበባ ለማሳለፍ ሲሞከር ነው። አሽከርካሪው የፖሊሶቹን እንቅሰቃሴ አንዳየ የተሽከርካሪውን  ቁልፍ ትቶ ለጊዜው ቢሰወርም፤ ቡናውና ገብሱ በኤግዚቢትነት ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ኅብረተሰቡ አጥፊዎችን በመጠቆም እንዲተባበርም አዛዡ ጠይቀዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም