በአጋሮ ከተማ የሰላምና ልማት ኮንፍራንስ እየተካሄደ ነው

63
ጅማ ኢዜአ ሀምሌ 8/2011  የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአጋሮ ከተማ አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት የሰላምና ልማት ኮንፍራንስ እየተካሄደ ነው። በኮንፍራንሱ  ከጅማ ዞን ጎማ ወረዳና አጋሮ ከተማ የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው። የተለያዩ የጥናት ፅሑፎች እንደሚቀርቡና  ውይይት እንሚደረግም ይጠበቃል። የኮንፍራንሱ ተሳታፊዎች የችግኝ ተከላ እንደሚያከናውኑ ታውቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም