ሴኔጋልና አልጀሪያ የአፍሪካ የዋንጫ ተሻሚዎች ሆኑ

78
አዲስ አበባ ኢዜአ ሀምሌ 8/2011 32ኛው የአፍሪካ የዋንጫ ትናንት ምሽት በተከናወኑ ሁለት ጨዋታዎች ለዋንጫው የደረሱት ቡድኖች ተለይተዋል፡፡ ምሽቱ ሁለት ጨዋታዎች ሴኔጋል ቱኒዝያን አንድ ለ ዜሮ በመርታት ለዋንጫ ስትደርስ  አልጀሪያ ደግሞ ናይጀሪያን ሁለት ለአንድ በመርታት ለዋንጫው ደርሳለች፡፡ ቱኒዝያ ከሴኔጋል ያደረጉት ጨዋታ ያለግብ የተጠናቀቀ ቢሆንም በተጨማሪው ሰዓት የቱኒዝያው ተከላካይ በራሱ ጎል ላይ ባስቆተራት አንዲት ጎል ቱኒዝያ ከዋንጫው ውጭ ስትሆን ሴኔጋል ለዋንጫ ቀርባለች፡፡ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የተከናወነው የናይጄሪያና የአልጀሪያ ጨዋታም በመደበኛው ሰዓት አንድ ለአንድ በመጠናቀቁ በተጨማሪ ሰዓት አልጄሪያ ባስቆጠችው አንድ ጎል ለፍጻማ መድረሷን አረጋግጣለች፡፡ በሁለቱም ጨዋታዎች ከመደበኛ ጊዜ ባለፈ በተጨማሪ ሰዓት ማለቁና ሁለቱም ጨዋታዎች ላይ በራስ ቡድን ላይ ጎል በስህተት በማስቆጠር ተመሳሳይ ሁኔታዎች ተስተውሎባቸዋል፡፡ በመጪው አርብ በካይሮ በሚጠናቀቀው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዋንጫ የቀረቡት አልጀሪያ እና ሴኔጋል የፍፃሜውን ጨዋታ ያከናውነሉ፡፡ ከዚህ የፍፃሜ ጨዋታ ቀደም ብሎ ከነገ በስቲያ ዕሮብ እለት ተሸናፊዎቹ ናይጄሪያና ቱኒዝያ የደረጃ ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የካፍ መርሃግብር ያሳያል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም