ዓለማቀፋዊ አስተሳሰብን በመላበስ ለአገሪቱ አንድነትና ብልጽግና እንደሚሰሩ ተመራቂ ተማሪዎች ገለፁ

70
አዲስ አበባ  ሀምሌ 6/2011 ከአገራዊ አስተሳሰብም በላቀ ዓለማቀፋዊ አስተሳሰብን በመላበስ የኢትዮጵያን አንድነትና ብልጽግና ለማጠናከር እንደሚሰሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ተማሪዎች ገለፁ። ድህነትን በመዋጋት ኢትዮጵያን ወደብልፅግና ጎዳና ማራመድ የሚቻለው አንድነትን በማጠናከርና ዓለማቀፋዊ አስተሳሰብን በመላበስ እንጂ በመለያየት አለመሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሩቃኑ ገልፀዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ9ሺህ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። በምረቃው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች ለአገሪቱ አንድነት እና ብልጽግና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተመራቂ ተማሪዎች ዓለም ወደአንድ መንደርነት በፍጥነት እየተለወጠች ባለችበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን፤ ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆነን በጋራ ለአገሪቱ ብልጽግና ልንሰራ ይገባናል ብለዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ምንጫቸው 'የዘረኘነት መርዝ' ነው የሚሉት ምሩቃኑ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር በሚደረገው ጥረት ውስጥ በተለይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተማሪዎች የበለጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላምና ደህንነት የ2ተኛ ዲግሪ ተመራቂዎቹ አቶ ነጋ ካሳ እና አቶ አቶ አራጋው ጥላሁን ለአገሪቱ እድገትና ብልጽግና መረጋገጥ 'ከጎጣዊ አስተሳሰብ' ይልቅ አለምአቀፋዊ አስተሳሰብ በመላበስ ለኢትዮጵያ አንድነት ልንሰራ ይገባል ብለዋል። በሶሻል አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ የሆኑት አቶ ያሬድ ዘገየ እና አቶ አብዮት ይገዙ በበኩላቸው የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ጠቃሚ እውቀትን ከመፍጠር ባሻገር አዕምሮንከጥላቻናከዘረኝነትያፀዳል፣አርቆማስተዋልንናሰብአዊነትንበማጎናፀፍምለሰውልጅደህንነትመቆርቆርንጭምርየሚያላብስመሆኑንጠቅሰው፤በዚህምመሰረትየሚጠበቅባቸውንለመወጣትቃልገብተዋል። መላው ዜጋም በቃላት ደረጃ የሚገልፀውን ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት በተግባር እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል። በህክምና ፊሲዮሎጂ የ3ተኛ ዲግሪ ተመራቂ የሆኑት ዶክተር እንደገና አበበ በበኩላቸው አሁን ላይ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ትምህርት ዋነኛው መሳሪያ በመሆኑ ምሁራን ለህብረተሰቡ ተምሳሌት በመሆን ዓለማቀፋዊነትን እና እድገትን ማምጣት የሚያስችል አቅም አላቸው ይላሉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9 ሺህ 637 ተማሪዎች ነው ዛሬ ያስመረቀው። በምረቃው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክትምሩቃን ማፍቀርን፣ መስጠትና ማገልገልን ትልቁ መርሃቸው አድርጋችሁ አገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።                  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም