በሱዳን ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል

71
ኢዜአ ሀምሌ 4/2011በሱዳን የነበረውን ተቋውሞ ተከትሎ ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተለቋል፡፡ ኢንተርኔቱ የተዘጋው በአገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት የሆነውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁን 3 በፀጥታ ሃይሎች እና ተቃዋሚዎች የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነበር፡፡ ኢንተርኔት በመዘጋቱ ክሱን ያቀረቡት የህግ ባለሙያው አብደል አዚም ሃሰን እንዳሉት የካርቱም አከባቢ ፍ / ቤት ዛየን ለተባለው ኩባንያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲለቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ለ37 ቀናት ተቋርጦ የቆየውን የኢንተንኔት አገልግሎት በከተማው መስራት መጀመሩን ተገልጿል፡፡ ፍርድቤቱ በተመሳሳይ ኤምትኤን እና ሱዳኒ ለተባሉ ተቋማትም ኢንትርኔት አገልግሎቱን እንዲለቁ ወስኗል፡፡ ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት የኢንተርኔት አገልግለቱን ክፍት እንዲያደርግ ግፊት ሲደረግበትም ቆይቷል፡፡ ወታደራዊ  የሽግግር መንግስቱ ከተቃዋሚዎች ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመር ከስምምነት ደርሶ እነደነበርም ተገልጿል፡፡ የመረጃው ምንጭ ዘ ኢስት አፍሪካ ኒውስ እና ሱዳን ትሪቡን  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም