ሊቢያ ስደተኞችን ጥቃት ከደረሰበት ማቆያ ማዕከል ነፃ እንዲወጡ ማድረጓ ተገለፀ

231

ሀምሌ 3/2011 ( ኢዜአ) የሊቢያ ባለስልጣናት ባሳለፊነው ሳምንት ትሪፖል አቅራብያ ባለችው ታጁራ ፊንዳታ ደርሶ ከነበረበት የስደተኞች ማቆያ ማዕከል ስደተኞችን በማስወጣት ላይ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዓዊ እና የስደተኞች ጉዳይ መግለፁን ታወቀ።

የጄኔራል ካህሊፋ ሃፍታር ታማኝ ወታደሮች አድርሰውታል በተባለው ጥቃት 50 ስደተኞች የተገደሉ ሲሆን የጄኔራሉ ታማኝ ሃይሎች ግን ለጥቃቱ መንግስትን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በአብዛኛው በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሳሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች እንደሆኑ ይታመናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የሊቢያ ባለስልጣናት ስደተኞችን ወደ ሌላ ማዕከል በማዛወሩ ረገድ ፈቃደኛ መሆናቸውን መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከ 310 በላይ ሰዎች ከአከባቢው የተንቀሳቀሱ ሲሆን 260 የሚሆኑት እንደልብ ለመንቀሳቀስ አመቺ ወደሆነው የስደተኞች ካምፕ እንደተሰባሰቡ መረጃው ጠቁሟል።

እንደ ዘገባ ኮሚሽኑ 55 ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞችን በመለየት ወደ ሌላ ሃገር ሊያስገባ የሚችል ቅድመ መረጃዎችን እንዲሟላላቸው እያደረገ ይገኛል።