መንግስት በክልልነት ጥያቄ ሽፋን ለሚነሱ ግጭቶችና ሁከቶች ትእግስት የለኝም አለ

141
አዲስ አበባ ሰኔ 24/2011መንግስት 'በክልልነት ጥያቄ ሽፋን' ለሚነሱ ግጭትና ሁከቶች ከዚህ በኋላ ትእግስት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 2010/2011 ዓ.ም የመንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት። መንግስት ክልል ልሁን የሚሉ ጥያቂዎችን በምን መልኩ ነው እየፈታ ያለው ለሚለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ምላሽ ስጥተዋል። ከደቡብምሆነከየትኛውምክልልየሚነሱጥያቄዎችንመንግስትደረጃበደረጃምላሽእንደሚሰጥ፤ ጥያቄ አቅራቢዎቹም ይህንን በትዕግስትእንዲጠብቁጠቅላይሚኒስትሩአሳስበዋል። ይህንን ወደጎን በመተው ከህግ ውጭ በመሆን 'በክልል እንሁን ሽፋን' የሚፈጠሩ ሁከቶችን ለመግታት መንግስት የሚወስደው እርምጃው የከፋ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ጠቅላይሚኒስተሩ አክዐውም "ሁሉምጥያቄዎችስርዓትንበጠበቀ መልኩ ይስተናገዳሉ"ብለዋል።              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም