ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የመጨረሻ ማጣሪያቸውን ነገ ያደርጋሉ

65
አዲስ አበባ ሰኔ 2/2010 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ነገ ከአልጄሪያ አቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ። 11ኛው የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ በመጪው ዓመት ህዳር በጋና አስተናጋጅነት ይካሄዳል። ሉሲዎቹ በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስፖርት ቤተሰቡ ጨዋታውን በነጻ ገብቶ እንዲከታተልና ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል። ሉሲዎቹ ከአራት ቀን በፊት አልጀሪያ አቅንተው 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈው መመለሳቸው ይታወሳል። በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ጎል ሳያስተናግዱ 2 ለ 0 ካሸነፉ ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው በቀላሉ በደርሶ መልስ አሸንፈው የሚያልፉ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ማጣሪያቸውን ከሊቢያ ጋር አድርገው በደርሶ መልስ 15 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈው ነው  ከአልጀሪያ ጋር የተገናኙት።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም