የኦሎምፒክ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ጋዜጠኞችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የእግር ኳስ ግጥሚያ አካሄዱ

66
መቀሌ ሰኔ 15 / 2011የኦሎምፒክ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በመቀሌ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጋዜጠኞችና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የእግር ኳስ ግጥሚያ አካሄዱ። የኦሎምፒክ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ዛሬ  በመቀሌ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በጋዜጠኞችና በኪነጥበብ ባለሙያዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር ተካሄደ። የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ያዘጋጀው ውድድር ጋዜጠኞች የኪነጥበብ ባለሙያዎችን 8 ለ5 በመሆነ ውጤት አሸንፈዋል። አሸናፊው ቡድን የተዘጋጀለትን ዋንጫ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ አንገሶም ካህሳይ ተረክቧል። አቶ አንገሶም ዋንጫውን ካስረከቡ በኋላ የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ስፖርትን የፍቅር፣ የሰላምና የአንድነት መሣሪያ መሆኑን ሊያስተምሩበት ይገባል ብለዋል። ጋዜጠኛ አወጣኸኝ ብርሃነ ኦሎምፒክ የስፖርት እምብርት ብቻ ሳይሆን የማይተዋወቁ ማህበረሰብ አባላት ስለሚያቀራርብ ጋዜጠኞች ህዝባዊና አገራዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብሏል። በአራት ዓመት አንዴ የሚከበረው የኦሎምፒክ ሳምንት በትግራይ ክልል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2011 ድረስ በፓናል ውይይት፣ በአትሌቲክስ፣ በቢስክሌትና በሌሎችም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ይከበራል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም