ኢራን የአሜሪካን ድሮን የመታችው በድንገት ይመስለኛል- ዶናልድ ትራምፕ

90
ሰኔ 14/2011ኢራን አሜሪካን የቅኝት አውሮፕላን (ድሮንን) መታ መጣሏ ትልቅ ስህተት እንደሆነ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ፡፡ “እንደሚመስለኝ ኢራን የአሜሪካ ድሮንን ሆን ብላ አቅዳ የመታች አይመስለኝም በድንገት ሳይታሰብ የሆነ የመስለኛል” ሲሉም ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ኢራን የአሜሪካ ድሮንን “ወደ አየር ክልሌ ጥሶ ገብቷል“ስትል መምታቷና መጣሏ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ውጥረቱ እያየለ ይገኛል፡፡ ኢራን” በአየር ክልሌ ሊሰልል በመንቀሳቀሱ ድሮኑን ልመታው ተገድጃለው “ስትል አሜሪካ “ውሸት “እያለች ትገኛለች፡፡ አሜሪካ ወደ ኢራን አየር ክልል ሳልገባ በሚፈቀድ ቦታ ላይ ነው ድሮኔ የተመታው ስትል የኢራንን ወቀሳ አልቀበልም ብላለች ፡፡ በሁለቱ አገራት መካከል የነበረው ውጥረት ወደ ለየለት ጦርነት እንዳይገቡ ብዙ አገራትን ስጋት ላይ ጥሏል ፡፡ የራሸያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን የሁለቱ አገራት ፍጥጫ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት ቢካሄድ ከፍተኛ ውድመትና ሊነገር የሚከብድ ቀውስ ይዞ ይመጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ሴክረተርያት አንቶንዮ ጎትሬዝ በበኩላቸው ሁለቱ አገሮች በፍጹም ወደ ጦርነት መግባት የለባቸውም ችግራቸውን ተነጋግረው መፍታት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ ምንጭ ፡-ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም