የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በግብፅ ካይሮ ይጀመራል

239

ሰኔ 14/2011 ለመጀመሪያ ግዜ 24 ቡድኖችን ያሳተፈው ሰላሳ ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በግብጽ ካይሮ ዛሬ ይጀመራል፡፡

በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ግብፅ ዙንባቤውን ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን በጸጥታና በዝግጅት ችግር ምክንያት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለግብጽ የተሰጣት መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ኪዘህ ቀደም በጥር ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮ ግን በሰኔ ወር እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

በግብጹ አፍሪካ ዋንጫ ካለው ሙቀት አንጻር  በ32 ተኛውና በ75 ተኛው ደቂቃ የውሀ እረፍት የሚኖረው ይሆናል ፡፡

ውድድሩ ከሰኔ 14 እስከ ሃምሌ 14 የሚካሄድ ሲሆን በስድስት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ እኤአ በ19 57 በሱዳን አዘጋጅነት የተጀመረ ሲሆን ግብጽ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ሳሙሄል ኤቶ አስራ ስምንት ጎል በማግባት የአፍሪካ ዋንጫ የምንግዜም ጎል አግቢ ነው፡፡

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ግብጽ ሰባት ግዜ በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን ብዙ ግዜ በማንሳት ቀዳሚ ነች፡፡

ምንጭ  ቢቢሲ