ግብጽ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ጋር በአዲስ አበባ ልትመክር ነው

60
ሰኔ /2011 የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆነችው ግብፅ  የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሀገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት በሚቻልበት ዙሪያ በአዲስ አበባ ሊወያዩ ነው። ሱዳን ትሪቡን  እንደዘገበው ያለፈው ሚያዝያ  ወር በካይሮ በተካሄደው የመጀመሪያ ወይይታቸው ወታደራዊው ምክር ቤት በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል ማስተላለፍ  እንዳለበት በመግባባት ተጠናቆ ነበር። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ እንደገለጹት ግብፅ ጥረት እያደረገች ያለችው ሁለቱ ሀይሎች በቀጥታ ድርድር አድርግው አከባቢው የተረጋጋ እንዲሆን ነው ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ፓርቲዎች ለሱዳን ትብብር፣ አንድነት እና መረጋጋት ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል በማለት አሀመድ አፈዝ  አክለው ተናግረዋል ። የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ደህንነት በኢጋድ የኢትዮጵያ መሪነት  በሱዳን ያሉ ፓርቲዎች በማደራደር ላይ ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ሐሙስ  ከሱዳን ካሉ  ፓርቲዎች ጋር በስምምነቱ ዙሪያ ይወያያሉ ተባሎ ይጠበቃል ። አራት ወር በፈጀው ህዝባዊ እምብተኝነት ባለፈው ሚያዚያ ወር ወደ ስልጣን የመጣው ወታደራዊ  የሽግግር  ምክር ቤት ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻለ ተጠቅሷል። ግንቦት 26/2011 የሱዳን ጦር ኃይሎች  በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ   ከ 100 በላይ ሰላማዊ ሰልፈኞች በመገደላችው ምክንያት በሁለቱ ወገኖች መካከል የነበረው ግንኙነት  እያሽቆለቆለ እንደመጣ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም