የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት በቤጂንግ ተመሰረተ

81
ሰኔ 13/2011 የመጀመሪያ ነው የተባለው የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት ቡድን በቻይና ሕዝቦች ፖለቲካዊ አማካሪ ጉባኤ አስተባባሪነት በትናንትናው ዕለት በቻናዋ ዋና ከተማ ቤጂንግ መመስረቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡ ይህ ቡድን መመሰረቱ በ2018 በቤጂንግ የተቋቋመውን የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ተግባራዊ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የቻይና ሕዝቦች ፖለቲካዊ አማካሪ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበርና የዚሁ ቡድን ሃላፊ  ዋንግ ዘሄነገዌ ገልፀዋል፡፡ ይህንን ጥሩ ጅማሮ በዕቅድና በጥናት በማገዝ ተልዕኮና ሃላፊነት የተሞላበት የአዲስ ዘመን የፖለቲካ አማካሪ ቡድን ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም