በክልሉ ከሚያስፈልጉ 187 ሺህ 543 ኩንታል የምርት ግብዓቶች በአብዛኛው ለአርሶ አደሮች ደርሰዋል- ቢሮው

49
አሶሳ ሰኔ 13/2011 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ2011/12 ምርት ዘመን ከታቀደው 187 ሺህ 543 ኩንታል የምርት ግብዓቶች በአብዛኛው ለአርሶ አደሮች መድረሳቸውን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ፡ በቢሮውየግብርናግብዓትምርትግብይትናየገጠርፋይናንስአገልግሎትተወካይአቶተስፋዬበቀለእንዳሉትበምርዘመኑ ከታቀደውየምርትግብዓቶች 120 ሺህ 864 ኩንታልለ80ሺህአርሶአደሮችደርሷል፡፡ ከምርት ግብዓቶቹ 102 ሺህ 204 ማዳበሪያ ሲሆን፣ቀሪው ምርጥ ዘር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምርት ግብዓቶች እየተሰራጩ ያሉት በ20 ወረዳዎች በሚገኙ የአርሶ አደር ኅብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒየኖች አማካኝነት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ ከመኸሩ እርሻ 395 ሺህ 610 ሜትሪክ ቶን የተፈጥሮ ማዳበሪያ በአርሶ አደሩ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንደሚውልበቢሮው የሰብል ጥበቃ ባለሙያ አቶ ደረጀ አየሩ አስረድተዋል፡፡ የአርሶ አደሩ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያ አቅርቦትና ዝግጅት እንደ ሰብሉ አመራረትና አጠቃቀም በቀጣይ ወራት እንደሚከናወንም አብራርተዋል፡፡ በአሶሳ ወረዳ የአምባ አምስት ቀበሌ አርሶ አደር ሰይድ ዓሊ ምርጥ ዘርና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተጠቅመው ማምረት ከጀመሩ ሶስት የምርት ዘመናትን እንዳሳለፉ ይናገራሉ፡፡ የምርት ግብዓቶችን በመጠቀም ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበታቸውን ቆጥበዋል። በሰብል በሄክታር የሚያገኙትን ምርት ደግሞ ከ10 ኩንታል ወደ 15 ኩንታል አድጓል፡፡ ዘንድሮም ካላቸው አንድ ሄክታር መሬት ግማሽ ያህሉን በቆሎ እያለሙበት ሲሆን፣ በቀሪው መሬት ደግም በአቅራቢያቸው ለሚገኘው የአሶሳ ገበሬዎች ዘይት ፋብሪካ በሽያጭ የሚያቀርቡትን ኑግ ለማምረት ማሳውን ማዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡ የማዳበሪያ ዋጋ መጨመር ዋነኛ ችግራቸው እንደሆነ አርሶ አደር ሰይድ ዓሊ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በአሁኑ ወቅት በቆሎና ማሽላ ሰብል በቡቃያ ደረጃ ሲገኝ ጤፍ፣ ለቦሎቄና ለጥራጥሬ ደግሞ የማሳ ዝግጅት እየተገባደደ ነው፡፡ በክልሉ በምርት ዘመኑ 34 ሚሊዮን ኩንታል ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም