በፖለቲካው መስክ የተመዘገበውን ድል በኢኮኖሚውም ለመድገም ተዘጋጅተናል- የምዕራብ ሐረርጌ ሕዝብ ተወካዮች

166

ጭሮ ሰኔ 4/2011 በለውጥ አመራር በፖለቲካው መስክ የተመዘገበውን ድል በኢኮኖሚውም ለመድገም መዘጋጀታቸውን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሕዝብ ተወካዮች ገለጹ።

በጭሮ ከተማ በኢኮኖሚ አብዮት ላይ ያተኮረ  የምክክር መድረክ ተካሂዷል። .

ተወካዮቹ  በኦሮሚያ  ክልል ብሎም በአገሪቱ የኢኮኖሚ አብዬት ላይ ባተኮረው ውይይት ላይ እንደተናገሩት ከአንድ ዓመት ወዲህ በአገሪቱ የተመዘገበውን ፖለቲካዊ ውጤት በኢኮኖሚውም ድል ለማስመዝገብ ሚናቸውን ይወጣሉ።

በዚህም የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ካሉበት ችግሮች ወጥቶ ዕድገት እንዲያስመዝግብ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

የበዴሳ ከተማ አቶ ረሺድ ከሊል ”ለለውጡ ከተዘጋጁ አመራሮች ጋር በመሆን በፖለቲካው ንቁ  ተሳትፎ እንዳሳየን ሁሉ፤ ፊታችንን ወደ ኢኮኖሚው ዘርፍ በማዞር ድሉን እንደግማለን። ለዚህም ተዘጋጅተናል”‘ብለዋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረህማን አብደላ በበኩላቸው የዞኑ ሕዝብ የአገሪቷን ብሎም የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።  .

በውይይቱ ከ15 ወረዳዎችና የሁለት የከተማ አስተዳደር ተወካዮች ተሳትፈዋል።.