ሀገሪቱን ከድህነት ለማውጣት አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ማስፋፋትና ወደ ሥራ ማስገባት እንደሚገባ ተጠቆመ

ሰኔ 2/2011 በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ሦስተኛው አገር አቀፍ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የጥናት ኮንፈረንስ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው። በዚህ ወቅት በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግርን የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጭ የቴክኖሎጂ ጥናቶች ቢካሄዱም ወደ ተግባር ሲገቡ አይታዩም፡፡ “ጥናቶች ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውንና ማህበራዊ እንቅስቃሴውን የማነቃቃት አቅም ቢኖራቸውም ተግባራዊ ስለማይደረጉ ምሁራንን ተስፋ ከማስቆረጥ ባለፈ ከድህነት አርንቋ እንዳንወጣ” አድርገዋል ብለዋል፡፡ መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በየዩኒቨርሲቲ የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ጥናቶችና አዳዲስ የፈጠራ ግኝቶችን በማስፋፋትና ወደስራ በማስገባት የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል ከድህነት ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የቴክኖሎጂ ሽግግርና እንቅስቃሴ ተሞክሯቸውንም ፕሮፌሰሩ በመድረኩ ለሙህራን አካፍለዋል፡፡ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ደሳለኝ ገዛኸኝ በበኩላቸው በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የመዕድን ሀብቶች ቢኖሩም በአጠቃቀም ጉድለት ምክንያት አገሪቱ ተጠቃሚ አለመሆኗን አመልክተዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ባደረጉት ጥናት በበቸላ ወንዝ ዳርቻ በርካታ የፔትሮሊየም ሀብት መኖሩን ገልጸዋል። "በአካባቢው ለአውሮፕላንና ለመኪና የሚሆን ነዳጅ ከመገኘቱ ባለፈ ሀብቱ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚውን ማሳደግ ይችላል "ብለዋል፡፡ እንደዶክተርደሳለኝገለጻ፣ፔትሮሊየሙመኖሩለበርካታዓመታትቢታወቅምእስካሁንተቆፍሮባለመውጣቱኢትዮጵያከሀብቱተጠቃሚመሆንአልቻለችም። “አሁንም መንግስት የሀብቱን መጠን በጥናት አረጋግጦ በማውጣት ከገጠመው የኢኮኖሚ ችግር ሊወጣ ይገባል” ብለዋል፡፡ “ጥናቶችና የፈጠራ ውጤቶች ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርሱ ዩኒቨርሲቲው የድርሻውን እየተወጣ ነው” ያሉት ደግሞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ነሲቡ ናቸው፡፡ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩና ችግር ፈች የሆኑ አምስት ጥናታዊ ጹህፎችን በማቅረብና በታዋቂ ምሁራን በማስተቸት ወደህብረተሰቡ ለማድረስ ማቀዱንም አስረድተዋል፡፡ በተማሪዎች የተሰሩ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችንም ለህብረተሰቡ እያደረሱ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ የመውቂያና ማጨጃ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ፣ የሲሚንቶ ማቡኪያ እና የጣውላ መሰንጠቂያ ማሽኖችን ተማሪዎች በአካባቢው ከሚገኙ ቁሶች በቀላሉ ሰርተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረጋቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ "ኮንፈረንሱ ላይ ተማሪዎች የሥራ ውጤታቸውን በማሳየትና ምሁራንም ጥናታቸውን በማቅረብ የልምድ ልውውጥ ከማድረጋቸው ባለፈ ጠቃሚ ግብአቶችን ለማግኘት ያግዛቸዋል" ብለዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት የኢንጅነሪግ ተማሪ እዮብ ብርሃኑ በበኩሉ በአየር ላይ እየዞረ ጸረ አረምኬሚካል በማሳ ላይ የሚረጭ ቴክኖሎጅ መስራቱን ተናግሯል። በርካታአርሶአደሮችየመርጫእቃተሸክመውእየዘሩኬሚካልበመርጨትጉልበታቸውንናጊዜያቸውንከማጥፋታቸውባለፈሲረጩማሳውንየሚዘሉበትሁኔታመኖሩለፈጠራስራውእንዳነሳሳውምአስረድቷል። የሰራው አዲስ የፈጠራ ስራ ለጊዜው 500 ሜትር በአየር ላይ ተንቀሳቅሶ የማሳውን ሁሉንም ቦታ እኩል ኬሚካል የመርጫት አቅም ያለው መሆኑን ተናግሯል። መሳሪያውን አርሶ አደሩ አንድ ቦታ ላይ ሆኖ ከርቀት መቆጣጠር የሚችል ሲሆን ቀጣይ እስከ አምስት ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ተንቀሳቅሶ ጸረ አርም ተባይ ኬሚካል መርጨት የሚችል የፈጠራ ስራ ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ መንግስት ድጋፍና እውቅና በመስጠት ከጎኑ እንዲሆንም ተማሪው ጠይቋል፡፡ በፌደራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስተር የኢኖቬሽን ልማት ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ኻሊድ አህመድ በበኩላቸው መንግስት ቴክኖሎጂዎችና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። “ከዚህ በፊት በርካታ ጥናቶችና አዳዲስ ግኝቶች ቢኖሩም በአጠቃቀም በኩል ክፍተት ነበር” ያሉት ዶክተር ኻሊድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአዲስ መዋቀሩ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከ50 እስከ 100 ሚሊዮን ብር ተመድቦ የሚሰሩ ጥናቶችና የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ማህበረሰቡ የማድረስ ስራ መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡ “በተመራማሪዎች የተረጋገጡ የመዕድን ሐብቶችንም በጥንቃቄ በመጠቀም የሥራ እድል ፈጠራውንና ኢኮኖሚውን የማሳደግ ስራም ይሰራል” ብለዋል፡፡ በዚህ ኮንፈረንስም በቀጣይ ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ከቴክኖጂጅው ጋር ትስስር ያላቸው በአገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 20 ጥናታዊ ጽህፎች እንዲቀርቡ መመረጣቸውን አስረድተዋል፡፡ ኮንፈረንሱ ለሁለት ቀን የሚቆይ ሲሆን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ሙህራንና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም