በአርባ ምንጭ በገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 110 ሱቆች ወደሙ

59
ሰኔ 2/2011 በአርባ ምንጭ ከተማ ሲቀላ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 110 ሱቆች ሙሉ ለሙሉ ወደሙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የእሳት አደጋው የደረሰው ትናንት ከምሽቱ 3፡30 ላይ ነው። ለአንድ ሰዓት በቆየው ቃጠሎ  110 የአልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥና መጠጥ መሸጫ ሱቆች ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ  በሰው ሕይወት ላይ አደጋ አለመድረሱ  ታውቋል ። የእሳት አደጋው ወደሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና መደበኛ ፖሊስ እንዲሁም የኢትዮጰያ አየር መንገድ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል። እስካሁን የአደጋው መንስኤና በአደጋው የወደመው የንብረት መጠን ባይታወቅም የማጣሪያ ቡድን ከፌዴራል ፎሬንሲኪ ዳሬክቶሬት እንዲመጣ ጥሪ መተላለፉን ኮማንደር ዳንኤል አስታቀዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም