የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ የሚያሰራጭ አካል እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል

67
አዲስ አበባ ግንቦት 30/2011  የጥላቻ ንግግርንና የሐሰት መረጃን የሚያሰራጭ አካል ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ። ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እንዲቻል በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከምሁራን፣ ከሚዲያ ባለሙያዎችና ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል። በውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ-ህጉ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንደገለጹት፤ በተለያዩ መንገዶች በሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና የሃሰት መረጃዎች ዜጎች ለሁከትና ለብጥብጥ ብሎም ለአላስፈላጊ እንግልት እየተዳረጉ ነው። ረቂቅ አዋጁም የጥላቻን ንግግርና ሃሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ ዜጎች ለአገር ሰላምና ለህዝቦች ደህንነት ጠንቅ በመሆናቸው ይህንን ለመከላከል የተዘጋጀ ነው። ረቂቅ አዋጁ “የጥላቻ ንግግር የሌላ ግለሰብን፣ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፣ ኃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን፣ ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋንና ውጫዊ ገጽታን፣ መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልኦና ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ነው" ብሎ ያስቀምጣል። ሃስተኛ መረጃን ደግሞ የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት የሆነና ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መሆኑንም ያመላክታል። በመሆኑም ግጭት በሚያስነሱና ጥቃት እንዲደርስ በሚያደረግ መልኩ ሆን ብሎ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃን ማሰራጨት የተከለከለ በመሆኑም ድርጊቱን በሚፈጽሙ አካላት ላይ ችግሩ እንድሚያስከትለው ጉዳት መጠን ከአንድ ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲሁም እስከ 100ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንምደሚያስቀጣ ተገልጿል። እንዲሁም ችግሩ እንደሚያስከትለው የጉዳት መጠን የማህበራዊ አገልግሎት ስራ እንደ ሌላ አማራጭ ቕጣት እንደሚወሰድም ተገልጿል። በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በአዋጁ የተቀመጠውን ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግም ሀላፊነት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በረቂቅ አዋጁ የተደነጉጉ ህጎችና ደንቦች ችግሩን ይቀንሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልዋል። ከዚሁጋርምችግሩንለመፍታትየሚሞከርበትመንገድየዜጎችንመብትያከበረሊሆንእንደሚገባምጠቁመዋል። በተለይም ችግሩ ከሚያስከትለው ጉዳት አንጻር በቅጣቱ ተፈጻሚነት ላይ ይበልጥ ትኩረት መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል። ዜጎችን በማስተማርና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድም መገናኛ ብዙሃን፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም አካላት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል። ፖለቲከኞች፣አክቲቪስቶችናሌሎችየማህበራዊሚዲያአገልግሎትየሚሰጡተቋማትናግለሰቦችምራሳቸውንበመፈተሽናበሚሰሯቸውስራዎችላይጥንቃቄበማድረግለአገርግንባታየበኩላቸውንመወጣትአለባቸውምነውያሉት።                              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም