የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በምርምርና በፈጠራ ስራዎች በመደገፍ ለልማት ማዋል ይገባል ተባለ

113

ግንቦት 29//2011 "በኢትዮጵያ የላቀ ቴክኖለጂን መጠቀም ድሎት ሳይሆን የድሆችን ህይወት መቀየሪያ መሳሪያ ነው" ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ኢትዮ ኢኖቬት 2019 የቴክኖለጂ ሳምንት በከፈቱበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት።

በኢኖቬሽንና ቴክኖለጂ ዘርፍ አቅም ያላቸውን ወጣቶችን  አሁን ለተጀመረው ለውጥ  እንደሚገባም ተናግረዋል።

በዘርፉ ሌሎች አገሮች የደረሱበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ውድድሩን ሳይውል ሳያድር በመጀመር "ከበይ ተመልካችነት" መላቀቅ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለዚህ ስኬት ዘርፉን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሰራበት ነው ብለዋል።

ዘርፉን ለማሳደግ የምናደርገው ጥረት ለድሎት መጠቀም ፈልገን ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩና በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህይወት ለመታደግ ነው ብለዋል።

የሰው ልጅ ተፈጥሮን ለኑሮ ምቹ ለማድረግና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማዘመን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ግድ ይለዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖለጂን በመጠቀም ግብርናውን ማዘመን፣ የተሻለ የጤና አገልግሎትና ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት ይገባልም ነው ያሉት።

የቴክኖለጂ ሳምንቱ "ኢትዮ ኢኖቬት" በሚል መሪ ሃሳብ ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም