ኢትዮጵያ የፊፋን ኮንግረስ ለማስተናገድ ተመረጠች

51

ግንቦት 28/2011 ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን 70ኛውን የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ኮንግረስ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።

 69ኛው የፊፋ ኮንግረስ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፖሪስ እየተካሄደ ነው።

የፊፋ አባል አገራት በታደሙበት በዚህ ኮንግረስ የኢትዮጵያ እክር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ምክትላቸው ኮሎኔል አወል አብዱራሂምና ዋና ፀሀፊው ዶክተር እያሱ መርሃጽድቅ ተሳታፊ ሆነዋል።

በዚህ ኮንግረስ ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት የሚካሄደውን 70ኛውን የፊፋ ኮንግረስ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም