የኢድ በዓል ተሳታፊዎች መልክት

63

ግንቦት 27/2011 የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአገራዊ አንድነትና ሰላም መስራት እንደሚገባ ተናገሩ። 

ከተለያዩ ስፍራዎች የተሰባሰቡት የእስልምና ኃይማኖት ምዕመናን 1440ኛውን የኢድ በዓል በአዲስ አበባ ስቴዲየም አክብረዋል።

እነዚሁ የእስልምና አምነት ተከታዮች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የዘንድሮ ኢድ በዓል በብዙ መልኩ በጋራ፣በአንድነትና በደስታ ያከበሩበት በዓል መሆኑን ያነሳሉ።

"ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት" ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ኢትዮጵያዊያን በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በቋንቋ ልዩነት ሳይገደቡ ኢትዮጵያን መገንባትና ሰላሟን ማረጋገጥ ያስፈልገናል ነው ያሉት።

በማንኛውም መስክ በእምነቱ ተከታዮች መካከል የሚደረግ መከፋፈል ለሃይማኖት ተቋማትም ለአገርም አይበጅምም ብለዋል።

አገራዊ ለውጡ ለህዝበ ሙስሊሙ አንድነትን ያመጣ መሆኑን የሚገልጹት ተሳታፊዎቹ፤ ከመንግስት ጎን በመቆም ለአገር ልማት፣ ለአንድነትና ለሰላም እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

በበጎ አድራጎት ስራዎችና የተቸገሩትን በመርዳትም በጋራ መቆም እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም