በመዲናዋ የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ መስፋፋት በንግድ ስርዓቱና በገቢ አሰባሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው

97

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2011 በአዲስ አበባ የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ መስፋፋት በንግድ ስርዓቱና በገቢ አሰባሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የከተማው ንግድ ቢሮ ገለጸ።

በመንግስትድጎማ የሚቀርቡ ሸቀጦችምቢሆኑ በታቀደላቸው መልኩ ለህብረተሰቡ እየደረሱ ባለመሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ ቅሬታ እያስነሳ መሆኑ ይታወቃል።

የከተማ ንግድ ቢሮ የንግድ ምርመራና ክትትል ክፍል ቡድን መሪ አቶ ሃብታሙ ጥላዬ ለኢዜአ እንዳሉት ህገወጥ ንግድ እየተስፋፋ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት አፋጣኝና የተቀናጀ ስራ ያስፈልጋል።

በመዲናው የንግድና ግብይት አሠራር ስርዓት ውስጥ የግልፀኝነትና የጥራት መጓደል እንዲሁም የዋጋ ንረት ዋነኞቹ ችግሮች ቢሆኑም የኮንትሮባንድና ህገ ወጥነት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑም ችግሩን ማወሳሰቡ በጥናት ተለይቷል።

በተለይ በዋና ዋና ምርቶች ላይ ክፍተኛ የደላላ ጣልቃ ገብነት መኖሩ፣መሰረታዊ ሸቀጦች በሚፈለገው ደረጃ ለህብረተሰቡ ያለመድረስና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ገበያና አገልግሎት መግባት ዋነኞቹ ናቸው።

ፀረ የንግድውድድር ተግባራት መፈፀም፣  ዋጋን በስምምነት መወሰን፣ ወቅት ጠብቀው ምርቶችን አለአግባብ ማከማቸት፤በተለይምበብረት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ በእህል ንግድ ላይ የሚታዩና ሀብረተሰቡን እያማራሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይ ያለደረሰኝ በሚሸጡና አየር በአየር በሚከናወን ንግድ መንግስትንም በሚሰበስበው ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያደረሰ ነው ብለዋል።

ለአብነትምባለፈው አስር ወር ከ15 ሺህበላይ የፓልም ዘይት፣ 253 ኩንታል ስኳር፣ 18 ኩንታል የድጎማ ዱቄትና ከ24 ሺህ ሊትርበላይ ቤንዚንና ናፍጣ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተይዞለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጉን ቡድን መሪው ተናግረዋል።

 ይህ ህገወጥ ተግባር ደግሞ በየዓመቱ የሚፈጸም ቢሆንምእነዚህንተቆጣጥሮየህብረተሰቡን ችግር የሚያቃልል መፍትሔ አለመገኘቱንም ነው የሚናገሩት።

የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ረገድ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ግን ይገልጻሉ። ለአብነትም ሸቀጦች ላይ አላስፋላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 123 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።

በከተማው ከ143 የሚሆኑ የሸማቾች ሀብረት ስራ ማህበራት ቢኖሩም ለህብረተሰቡ በበቂ ሁኔታየሚፈለገውን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።ለዚህምማህበራቱን በአግባቡ እያስተዳደሩ በበቂ ሁኔታለህብረተሰቡ ምርት የሚያቀርቡበትን አሰራር መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይ በህወጥ ንግድ ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ወጥ አለመሆንና የአስፋጻሚ አካላት አቅም ማነስእንዲሁምየተደራጀ ግብረኃይል በወረዳ ደረጃ አለመኖሩ ደግሞ ችግሩን ለማስወገድ እንዳይቻል ተግዳሮት መሆኑን አልሸሸጉም።

በመሆኑምመንግስታዊ አቅምን በማጠናከር፣ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትንበማሳተፍ በአጭር በመካከለኛና ረዥም ጊዜ እቅዶችን አስቀምጦ ችግሮቹን ጊዜ ሳይሰጥ መፍታት ይገባዋል ብለዋል።

በመንግስት ከፍተኛ ድጎማ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የሀብረተሰብ ክፍል ለመጥቀም ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ላልተገባ ጥቅም እየዋሉ መሆኑን የሚያነሱት ቡድን መሪው፤ በንግድ ስራው ላይ የደላላ ጣልቃ ገብነት የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ እያናጋና ለመንግስት ግብር እየከፈለ የሚሰራውን ነጋዴን ጥቅም እየጎዳ በመሆኑ በዚህ ላይ በሰፊው ሊሰራ ይገባልም ይላሉ።

ቢሮው የአስቸኳይ ጊዜ እቅድ በማውጣትና ከተለያየ ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ግብረሃይል በማቋቋም ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን  አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም