የሱዳን የደህንነት ቢሮ በሀገርቱ እየተፈጠረ ያለውን ግጭት እንደሚያስቆም ተነገረ

182

ግንቦት 23/2011 የሱዳን የደህንነት ቢሮ በቅርብ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ሰላማዊ ዜጎች በመገደላቸው  እየተፈፀመ ያለውን አመፅ እንደሚያስቆም ተነገረ፡፡

የደህንነት ቢሮው የሱዳን ጦር ኃይሎች፣ የፖሊስ ኃይሎች፣ የብሔራዊ መረጃ እና የደህንነት አገልግሎት እና የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎችን ያካተተ እንደሆነ በመረጃው ሰፍሯል።

የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ  ህግ እና ስርዓትን  መሰረት ባደረገ መንገድ የደህንነት ሰራው  እንደሚከናወን የሱዳን መከላከያ ቢሮ በመግለጫው ተናገሯል።

የድህንነት በሮው ዜጎች ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ወደ አመፅ ሊወስዱ የሚችሉ ክስተቶችን ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል።

እንደ ዘገባው የደህንነት ቢሮ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት  ነፃነት፣ ሰላም እና  ፍትህ ለማስፍንም እንደሚሰራ ገልፅዋል።

ካለፈው ሚያዝያ 6 ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ተቃዋሚዎች እያደረጉበት ባለው  በካርቱም የሠራዊቱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አቅራቢያ ባለፉት ሁለት ቀናት  የደህንነት አደጋ ተፈጥሮ እንደነበር በዘገባው ሰፍሯል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር ከተወገዱ በኋላ የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል-ፋታህ አል-ቡርሃን  አገሪቱን የማስተዳደር  ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ይታወሳል ሲል ዥንዋ በድረ ገፁ አስነብቧል።