''በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ከምሁራን የላቀ ሚና ይጠበቃል''-ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ

91

ጋምቤላግንቦት 16 /2011 በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከምሁራን የላቀ ሚና እንደሚጠበቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስገነዘቡ።

የክልሉ ምሁራን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ ውይይት አካሄደዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሳሰቡት የክልሉ ምሁራን ሙያና  ልምዳቸውን  በመጠቀም  ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ለልማትና እድገት መፋጠን ሊሰሩ ይገባል።

ለዚህም ምሁራን በተለይም ክልሉን እየተፈታተነው ካለው የብሄርተኝነትና የጎሰኝነት አስተሳሰቦች መውጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል። 

በክልሉ በየጊዜው የሚከሰቱ የብሄር ግጭቶች የሚወገዱት ልዩነቶችን በማጥበብ አብሮ የመኖር እሴቶችን በማጠናከር ነው ብለዋል።

አንዳንድ ምሁራን ብሄርን ተገን በማድረግ ችግር ሲፈጥሩ መቆየታቸውን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ችግር ፈቺ ሃሳቦችን በማፍለቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበዋል። 

ከመድረኩ ተሳፊዎች መካክል ዶክትር ማኝ ኛንግ በሰጡት አስተያየት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ያልተረጋገጠው የህግ የበላይነት ባለመከበሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

የሰው ህይወት ያጠፋ ወንጀለኛ በህግ ካልተጠየቀ፤  ሰላም  ማስፈን  እንደማይቻልም  ነው የተናገሩት። 

ለጋምቤላ ክልል የሰላምች ግር ዋነኛው ምክንያት  የብሄር የበላይነት ስሜት ማደግ  መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌለው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ አብርሃም ማይከል ናቸው።

ስለሆንም ከነዚህ የብሄረተኝነትና የጎሰኝነተ አስተሳሰቦች  ራስን ማጽዳት  እንደሚገባ አመልክተዋል።

ሌለው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ ካንግ ኩልንግ በሰጡት  አስተያየት በክልሉ  ባለፉት  ዓመታት የተከሰቱ ግጭቶች ከህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም በስተቀር ያስገኙት ጥቅም እንደሌለ ገልጸዋል።

በአንዳንድ ምሁራን  የሚስተዋሉ ግጭቶችን  ከሚያባብሱ ችግሮች  መውጣት  አለባቸው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምሁራኑ ለተነሱት  ሃሳቦች በሰጡት ምላሽ በክልሉ  የህግ  የበላይነትን  በማረጋገጥ ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን  አምነው፣  ክፍተቶቹን  ለማረም የምሁራን ተሳትፎ እንዲታከልበት ጠይቀዋል። 

በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለአንድ ቀን በተካሄደው  የውይይት  የተሳተፉት  ምሁራን ከትምህርት ተቋማትና ከመሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ ናቸው።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም