የኦሮሞና አፋር ህዝባዊ ኮንፍረንስ ለሚሳተፉ ልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገ

78

ግንቦት 15/2011 የኦሮሞና አፋርን ትስስር ለማጠናከር በአዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ ነገ በሚካሄደው ህዝባዊ ኮንፍረንስ ለመሳተፍ የመጡ የአፋር የልዑካን ቡድን አባላት ደማቅ አቀባበል ተደረገ።

በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የተመራው ህዝባዊ የልዑካን ቡድን አባላት  ዛሬ አዳማ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ያደረገላቸው  የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።

በኮንፍረንሱ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና ከኦሮሞና አፋር ህዝቦች የተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች  ጨምሮ ከ2ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ለዝግጅቱ ከወጣው መርሀ ግብር ማወቅ ተችሏል።

የአፋርና ኦሮሞ ህዝቦች ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን የዳሰሱ ዕሁፎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

ከአፋር ክልል ለመጡት የልኡካን ቡድን በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የትውውቅና የእራት ፕሮግራም መዘጋጀቱም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም