በአጭር ርቀትና በሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ተግባራት የሚወዳደሩ አብዛኛዎቹ ስፖርተኞች የልምድ ተወዳዳሪዎች ናቸው

61

ግንቦት 14/ 2011 በአጭር ርቀትና በሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ተግባራት የሚወዳደሩ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የልምድ ተወዳዳሪዎች ናቸው ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ።

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስታውቋል። 


ኢትዮጵያ በረጅም ርቀት የምትታወቅ ቢሆንም በአጭር ርቀት እንዲሁም ውርወራና ዝላይንበመሳሰሉየሜዳ ላይ ስፖርታዊ ተግባራትበዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ እጅግ የመነመነ ነው።

ለዚህም ዋናው ምክንያት በውድድሮቹ ዓይነት የበቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት በአገሪቱ ያለው የባለሙያ እጥረት ዋናው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይገልፀሰሉ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንየቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢዜአ የገለፁትም ይህንኑ ነው።

እርሳቸው እንዳሉት በኢትዮጵያ በአጭር ርቀት ፣በመሰናክል፣ በዝላይና ውርወራ ስፖርቶች የሚወዳደሩ አብዛኞቹ አትሌቶች በልምድ ባገኙት እውቀት የሚወዳዳሩ ናቸው፤ ለዚህም ዋናው ምክንያት አብዛኞቹ የክለብ አሰልጣኞች ዘመናዊ ስልጠና የማይሰጡ በመሆናቸው መሆኑን ነው። 

በአጭር ርቀት፣ በሜዳ ተግባራትና በመሰናክል ሩጫ ላይ ከተወሰኑ ክለቦች ከመጡ አትሌቶች በቀር ብዙዎቹ በቴክኒክ በኩል ደካማ መሆናቸውን ነው የገለጹት። 

ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው 48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይም ይህ ችግር የተንጸባረቀበት እንደነበር ነው የተገለጸው።

በቀጣይ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት የሩጫ ውድድሮች ውስጥ የ10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ውድድርች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጣቸው ትኩርት እየቀዘቀዘ በመምጣቱ በአጭር ርቀትና በሜዳ ተግባራት የፌዴሬሽኑ የትኩርት መስክ መሆኑንም አመልክተዋል። 
በዚህ ዓመት ከጀርመንና ከደቡብ አፍሪካ አሰልጣኞች በማምጣት የአሰልጣኞች ስልጠና ለመስጠት እንደታሰበ ነው የተናገሩት።
አሁን ያለው የአትሌቶች የምልመላ ስርዓቱ ችግር ያለበት በመሆኑ ይሄን በማስተካከል ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ነው ያብራሩት።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም