አምባሳደር ተስፋዬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ አቀረቡ

67

አዲስ አበባ ግንቦት 13/2011 በአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኮሚሽኑ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ቬራ ሶንግዌ አቅርበዋል

አምባሳደር ተስፋዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና ኢትዮጵያ ከ60 በላይ ዓመታትን የተሻገረ ትብብር እንዳላቸው አውስተዋል።

ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ ጋር ያላት መስተጋብር የበለጠ እንዲጠናከርም አበክረው እንደሚሰሩም አምባሳደር ተስፋዬ ለዋና ጸሃፊዋ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ምላሽና እገዛ እንደሚያደርግም አረጋግጠውላቸዋል።

ዋና ጸሃፊ ዶክተር ቬራ ሶንግዌ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ላለፉት በርካታ አመታት ትኩረቱን የንግድና ኢኮኖሚ ጉዳዮች አድርጎ በዴሞክራሲም ጭምር ከኢትዮጵያ ጋር ጠቃሚ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አውስተዋል።

በቀጣይም እነዚህንና መሰል ተግባራቱን አጠናከሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም