የአውሮፓ ህብረትና ቻይና በሲቪል አቬሽን ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

50

ግንቦት 13/2011 የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንና ቻይና በአካሄዱት የጋራ ስብሰባ በሲቪል አቬሽን ዘርፉ በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ስምምነቶችም በበረራ ደህንነት እና በተወሰኑ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ፕሬዚዳንት ጅን ክለድ ጁንከር እንደገለፁት ይህን መሰል ስምምነት በአውሮፓ ህብረትና ቻይና መካከል ሲካሄድ የመጀመሪያውና ትልቅ የተባለለት እርምጃ ሲሆን አለም በተለያዩ ውጥንቅጦች ውስጥ በገባችበት በአሁኑ ጊዜ መደረጉ ደግሞ ከምንም ጊዜ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

"የአውሮፓ ህብረት የሃገራት በትብብር መስራት ጠንካራ፣ ደህንነቷ የተጠበቀና የበለፀገች አለም ለመፈጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በፅኑ ያምናል” ብለዋል ፕሬዘዳንቱ፡፡

ሁለቱ ስምምነቶች “በስራ እድል ፈጠራ፣ እድገትን በማፋጠንና የህዝብ ለህዝብ ቅርርብን በማጠናከር የጎላ ድርሻ ስላላቸው ለወደፊቱም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው” ሲሉም ጁንከር ጨምረው ገልፀዋል።

የቻይናው የሲቪል አቬሽን መስሪያ ቤት ፕሬዘዳንት የሆኑት ፈንግ ዠንግሊን በበኩላቸው የተፈራረሙባቸው ሁለቱ ስምምነቶች በቀጣይ ለቻይና እና ለአውሮፓ ህብረት በሲቪል አቬሽን ዘርፍ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር ለሰትራቴጅካዊ አጋርነታቸው ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል መባሉን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም