ምክር ቤቱ የኢዜአ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማስፈፀም የቀረበ ረቂቅ ደንብ ለቋሚ ኮሚቴ መራ

106

አዲስ አበባ ግንቦት 13/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማስፈፀም የወጣ ረቂቅ ደንብን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለህግ ፍትህና ዲሞከራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መራ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማስፈፀም የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

ደንቡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ወደ ሥራ  ለመተርጎም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል።

ተቋሙ ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር የአገሪቷን ገጽታ የመገንባት ተልዕኮውን  በብቃት መወጣት እንዲችል ዝርዝር ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ለምክር ቤቱ አባላት ተገልጿል።

የምክር ቤቱ አባላት በደንቡ አስፈላጊነት ዙሪያ ያላቸውን ገንቢ አስተያየት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የወጣውን  ረቂቅ  ደንብ  የህግ  ፍትህና  ዲሞክራሲ  ጉዳዮች  ቋሚ  ኮሚቴ በዝርዝር እንዲያየው መርቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም