የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት በአዲስ አበባ በሁለት ፈረቃ እንዲሆን ተደረገ

70

ግንቦት 13/2011 በኃይል እጥረት ሳቢያ  በአዲስ አበባ በሶስት  ፈረቃ  ይሰጥ  የነበረው  የኤሌከትሪክ ሃይል ለአሰራር ምቹ ባለመሆኑ በሁለት ፈረቃ እንዲሆን  መወሰኑን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ የኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር  አቶ መላኩ  ታዬ  ለኢትዮጵያ ዜና  አገልግሎት  እንዳሉት ፈረቃው ከንጋቱ 11:00 እስከ ቀኑ 8:00  እና ከቀኑ 8:00 እስከ ምሽቱ 4:00  እንዲሆን  ተደርጓል።

በሁለቱ የፈረቃ ሰዓቶች በመቀያየር ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን  ጠቁመዋል።

በከተማዋ የውሃ መስመሮች ሆስፒታሎች የምግብ ማቀነባባሪያዎች፣ ዩንቨርስቲዎችና  በሌሎችም አገልግሎት መስጫ ተቋማት መብራት እንዳይቋረጥ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከፈረቃቸው ወጪ የመብራት አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማድርግ ተቋሙ እየሰራ  መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በተለይ ባረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ በንፋስ፣ በዝናብና በሌሎች ሰው ሰራሽ ችግሮች ሳቢያ ለሚከሰት የሃይል መቋረጥ አስቸኳይ ጥገና ለመስጠት እየተሰራ ነው ተብሏል።

በክልሎችም ያለውን መርሃ ግብር በዲስትሪክትና አገልግሎት መስጫ ጽህፈት ቤቶች  የሚገለጽ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም