የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዝርዝር ይፋ ተደረገ

147

ግንቦት 13/2011 የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዝርዝር ይፋ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የፈንዱን አጠቃላይ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ቁጥጥርና ተጠያቂነት የሚያስተዳድር የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ራስ ነው።

ከሥራዎቹም መካከል በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ተለይተው የሚታወቁ እና የተረጋገጡ ፕሮጀክቶችን ድጋፍ ይመረምራል፣ ያጸድቃል።

በመሆኑም አሥራ አንድ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የሲቪል ማኅበራትና የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ያሉት ይኸው ቦርድ ይፋ ተደርጓል።

1. በየኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ አባላት የተመሰከረላቸው አምስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣

2. ሦስት ከሴቶች፣ ከወጣቶችና ከኢትዮጵያ ነዋሪዎች የተውጣጡ አባላት ያሉት የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮችና፣

3. ሦስት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ይገኙበታል።

በዚህም መሠረት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፤

1- ሥርጉት ያደታ፥ ሎይድ ባንክ ግሩፕ

2- ዶ/ር ምሕረት ማንደፍሮ፥ ትሩዝ ኤይድና ቃና ቴሌቪዥን

3- ቸርነት ደበሌ፥ ኪያ ትራቭል እና ቢዝነስ

4- ዮሐንስ አሰፋ፥ ዮ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ

5- ዶ/ር አብዱልዋሀብ ኢብራሂም አቡዳቢ

6- ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፥ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ

7- የወጣቶች ተወካይ በቦርድ ታይቶ የሚወሰን ይሆናል

8- ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ፥ ኅብረት ባንክ

9- ሰላማዊት ዳዊት፥ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ

10- ሂሩት ዘመነ ፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት

11- ብሌን ማሞ፥ ገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት

ቦርዱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎች አባላትን ይመርጣል ተብሏል።

በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ማህበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ ልማት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት ይችሉ ዘንድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ አነሳሽነት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የዛሬ ዓመት ገደማ መቋቋሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም