የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ እጥረትና መፍትሄዎቹ በምሁራን እይታ

201

አዲስ አበባ ግንቦት 12/2011 የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻው ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የመጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻው አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።

ችግሩን በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ለመፍታት ያስችላሉ ያሏቸውን የመፍትሄ ሀሳቦችንም ምሁራኑ ጠቅሰዋል።

በዓለም የትኛውም አገር ራሱን ችሎ ከሌሎች አገሮች ጋር ሳይገበያይ ተነጥሎ መኖር አይችልም።

የግብይት መጠኑና አይነቱ ይለያይ እንጂ አንዱ አገር ከአንዱ የሚወስደው አንዱ ለአንዱ የሚሰጠው ምርትና አገልግሎት (ሰጥቶ መቀበል) አለ።

ይህን ግብይት ለመፈጸም ደግሞ የየአገሮቹ የመገበያያ ገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ኢትዮጵያም መድሃኒትና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶችን ከተለያዩ አገሮች በስፋት ከሚገበያዩ አገሮች መካከል አንዷ በመሆኗ የሌሎች አገሮችን ገንዘቦች ማግኘት ይኖርበታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት መምህርና የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ዶክተር ብርሃኑ ደኖ የውጭ ምንዛሬ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው

ኢትዮጵያ ብዙውን ጊዜ የውጭ ምንዛሬን የምታከማቸው ከውጭ አገሮች በብድርና በእርዳታ ከምታገኘው ገቢ፣ ከቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ከዳያስፖራ ነው።

ይሁንና ባለፉት አራትና ሶስት ዓመታት በአገሪቷ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተባባሰ መምጣቱን ነው የሚናገሩት።

በአገሪቷ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በየጊዜው የሚያጋጥም ቢሆንም ባለፉት ሶስት ዓመታት በተለያየ ሁኔታ ከውጭ የሚገባው የውጭ ምንዛሬ መቀነሱን ዶክተር ብርሃኑ ያስረዳሉ።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ሙስና እና ህገ ወጥ  የገንዘብ  ዝውውር  መሆኑን  በመጥቀስ።

በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የኢኮኖሚ ምሁር ዶክተር ወንዳፈራሁ ሙሉጌታ ደግሞ የግብርና ምርቶችን በመጠንና በአይነት ያለማሳደግና ምርቶች ላይ እሴት አለመጨር ለእጥረቱ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ።

ደግሞ የግብርና ምርቶችን በመጠንና በአይነት ያለማሳደግና ምርቶች ላይ እሴት አለመጨር ለእጥረቱ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ።

በተለያዩ አከባቢዎች የተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸውወደ ስራ አለመግባታቸው ሌላው ምክንያት መሆኑንም እንዲሁ።

የአገሪቷን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በአጭር በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ለመፍታት ሊሰሩ ይገባቸዋል ያሏቸውን የመፍትሄ ሀሳቦችንም ምሁራኑ አስቀምጠዋል።

ከውጭ የሚገቡ የቅንጦት ዕቃዎችን መቀነስና የኮንትሮባንድ ንግድን መቆጣጠርም ሌላ መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለያዩ አገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠርና ባለሃብቶችን መሳብ ላይ በትኩረት መስራት አለባቸውም ነው ያሉት።

የስኳር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን ለግል ዘርፍ እንዲዘዋወር ማድረግ እንዲሁም ግብርናውን ማዘመን ችግሩን በመካከለኛ ጊዜ ለመፍታት እንደሚረዳም ጠቁመዋል።

ከጎረቤት አገሮች ጋር በልማት መተሳሰርና የንግድ ልውውጡን ማጠናከር፣የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንዲሁም የማዕድን ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ሌላው አማራጭ ነው።

የአንድ አገር የውጭ ምንዛሬ ክምችት አስተማማኝ ነው የሚባለው የ9 ወር ወይም የ6 ወር መጠባበቂያ ሲኖር መሆኑን መረጃዎች ያለመክታሉ።

ለሶስት ወር መጠቀሚያ የሚበቃ ክምችት ካለም በቂ ነው የሚባል ሲሆንከሁለት ወር ያነሰ ግን አስጊ መሆኑን ምሁራኑ ገልጸዋል።

የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ከሳምት በፊት አሁን አገሪቷ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬን እንድትጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ አለመሆኗንና በቂ ክምችት እንዳላት መናገራቸው ይታወሳል።

አሁን ከ2 ነጥብ 6 ወራት በላይ የሚሆን ክምችት ያለ ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላ ግን ክምችቱ አይኖርም ማለት አለመሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

የአገሪቷን የውጭ መንዛሬ ክምችት ለማሳደግ ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ ገቢ እንዳለ ሆኖ የአገር ውስጥ ቁጠባን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ምሁራኑ ጠቁመዋል።