ቦይንግ የ737 ማክስ ሲሙለተር( ምስለ በረራ) ችግር እንደነበረበት ገለፀ

278

ግንቦት 11/2011 ቦይንግ የ737 ማክስ ምስለ በረራ ችግር እንደነበረበት ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው ሪፖርት ማመኑን ኤኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

“ቦይንግ በ737 ምስለ በረራ ሶፍትዌር ላይ ማሻሻያ አድርጓል፣ይህም ምስለ በረራውን ለሚጠቀሙ ተጨማሪ መረጃዎችን በመስጠት በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ለመብረር የሚያስችላቸውን ልምድ ይሰጣል” ብሏል ቦይንግ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጠው መግለጫ ፡፡

ቦይንግ እንዳሳወቀው የምስለ በረራው ችግር በኢትጵያም ሆነ በኢንዶኔዢያ አጋጥሞ የነበረውን አደጋ ለመቆጣጠር የሚያስችል አልነበረም ፡፡

በሁለቱ ሃገራት ከደረሰው አደጋ በኋላ የማከስ 737 አውሮፕላኖች በአለም አቀፍ ደረጃ መታገዳቸው ይታወሳል ፤ለ346 ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነው አደጋም በቦይንግ የሶፍት ዌር ችግር መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ቦይንግ ሲሙለተሩ ላይ ያጋጠመው ችግርን መቼ እንዳወቀ ይፋ አላደረገም ፡፡