የፅዳት ዘመቻው አካባቢን ንፁህ ከማድርግም ያለፈ ፋይዳ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለጹ

57

ግንቦት 11/2011 የአካባቢ ፅዳት ተላላፊ በሽታዎችን ከመከላከል ባሻገር ጥሩ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ኢዜአ ያነጋገራቸው የፅዳት ተሳታፊዎች ተናገሩ። 
በተለያዩ የአካባቢዎች ሰላም፣ እድገተና የፀጥታ ጉዳዮቻቸው ላይ በጥምረት እንዲሰሩ ለሚከሰቱ ችግሮም የጋራ የምፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ ያግዛል ነው የሚሉት።

ከአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በዘመቻው ላይ ሲሳተፉ ያገኝናቸው አቶ ግርማ ገመቹም ከአሁን በፊት የፅዳት ልምድ ደካማ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ካለፉት አመታት ተሞክሮዎች ማየት እንደሚቻለው የጽዳት ዘመቻዎች አብዛኛውን ሕብረተሰብ ያላሳተፉ ነበሩ።

አሁን ግን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈና የመንግስት ሃላፊዎችም ጭምር እየተሳተፉበት በመሆኑ ለውጥ እንደሚያመጣና ጥሩ ውጤት እንደሚመዘገብበትም ገልጸዋል።

የአካባቢ ጽዳት ከየአንዳንዱ ሕብረተሰብ አስተሳሰብ የሚጀምር ነው ያሉት ደግሞ በፅዳት ዘመቻው ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው አቶ ሚካኤል ወርዶፋ ናቸው።

የፅዳት ዘመቻው በየደረጃው ከሌሎች ጉዳዩች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያያዝ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ዘመቻው አካባቢን ፅዱና አረንጓዴ ከማድረግ ባለፈ ብሩሕ አእምሮ ያለው ትውልድ ለመፍጠርና የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚን ለማሳካት እድሎችን ይፈጥራልም ተብሏል።

በአዲሰ አበባ በተከናወነው የፅዳት ዘመቻ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም