በጎ አስተሳሰብን በማጎልበት ለአገር ሰላም መስራት ያስፈልጋል- ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል

114

ግንቦት 11/2011 የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ኢትዮጵያውያን በጎ አስተሳሰብን በማጎልበት ለሰላም ግንባታ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠየቀ።
ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ከሚል በሁለተኛው የአገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ከተቋሙ ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ከወሎ ሰፈር እስከ ጎተራ ማሳለጫ መንገድ አፅድተዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያ ት በዚሁ ጊዜ ለኢዜአ እንዳሉት የአካባቢ ንጽህና በጎ አሰተሳሰብ ለመያዝ ትልቅ ፋይዳ አለው።

"በጎ አስተሳሰብ ለሰላም አንድ መግቢያ በር ነው" ያሉት ሚኒስትሯ የቆሸሹ አስተሳሰቦችን በማስወገድና በጎ አስተሳሰብን በማጎልበት ለአገር ግንባታ መስራት ይገባል ብለዋል።

"ሰላም በእያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ እንዲኖር ለሌሎች በጎ አስተሳሰብን በማጎልበት ለአገር ሰላምና አብሮነት የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል" ሲሉም መልክት አስተላልፈዋል።

እያንዳንዱ ሰው ሰላም ለራሱ ሲሰጥ ለጎረቤቱ፣ ለአካባቢውና ለአገሩ የሚተርፍ ይሆናልም ብለዋል።

ሰላም በሁሉም የህብረተሰብ እጅ የሚገኝ በመሆኑ የዘረኝነት አስተሳሰብን በማስወገድ ለአካካቢና ለአገር ሰላም መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ጥላቻን፣ ዘረኝነትን፣ መከፋፈልን፣ ቂምን ለማስወገድ መወሰንን በእያንዳንዱ ሰው እጅ ያለ ጉዳይ በመሆኑ እርስ በእርስ በመዋደድ እያንዳንዱ ሰው ለሌሎች በጎ አስተሳሰብ እንዲያጎለብት ጠይቀዋል።

በዘላቂነት አካባቢውን ለማልማት ፕሮጀክት ዲዛይን መጠናቀቁን ገልጸው በዛሬው እለት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ አላማ በጎ አስተሳሰብን በማጎልበት ሰላም በበጎነት ውስጥ እንደሚገኝ ለማስተማርና የሰላም እሴቶችን ለማስተዋወቅ ነውም ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በቋሚነት የሚሰራ ሲሆን ሁልጊዜ በሳምንትና በወር የሚካሄድ ይሆናል።

አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ቂም፣ ጥላቻን በማስወገድ የአስተሳሰብን የማጽዳት አላማ ያለው በመሆኑ ሚኒስቴሩ ለሚሰራው የሰላም ግንባታ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም