ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ና ወላይታዲቻ ባዶ ለባዶ ተለያዩ

186

መቐለግንቦት 10/2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር  ሊግ  ዛሬ  የተገናኙት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና ወላይታ ዲቻ አቻ ተለያዩ።

በሊጉ 25ኛ ሣምንት ጨዋታ መቀሌ ላይ የተጫወቱት ክለቦች አቻ የወጡት ያለ ምንም ግብ በመለያየታቸው ነው።

ውጤቱን ተከትሎ  ወልዋሎ ዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ35 ነጥብ ሰባተኛ፤ ወላይታ ዲቻ ደግሞ በ28 ነጥብ12ኛ ደረጃ ላይ  ተቀምጠዋል።

ሊጉን መቀሌ ሰባ እንደርታ በ48 ነጥብ ሲመሩ፣ዳሲል ከነማና ሲዳማ ቡና ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

የሊጉን ዋንጫዎች ከ10 ጊዜ በላይ የወሰደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ደቡብ ፖሊስ፣ስሁል ሽረና ደደቢት ከ14ኛ እስከ 16ኛ ደረጃዎች በመያዝ በወራጅ ቀጣና ውስጥ ናቸው።