አብያተ ክርስቲያናት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን በህዝቦች ሰላምና ፍቅር ላይ በቋሚነት ሊሰሩ ይገባል

65

ግንቦት 10/2011 አብያተ ክርስቲያናት ከሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን በህዝቦች አብሮነት ሰላምና ፍቅር ላይ በቋሚነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

የኢትዮጵያን ሰላም ለማረጋገጥ አብያተ ክርስቲያናት ቀደም ሲል የሚያከናውኑትን ተግባራት የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።


በኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ ማህበር አዘጋጅነት ''ሰላምና እርቅን ለማስፈን የአብያተ ክርስቲያናት ሚና'' በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።


በዚሁ ጊዜ ሰላምና እርቅን በማምጣትና የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በመለወጥ ረገድ አብያተ ክርስቲያናት እስካሁን ሲያከናውኑ የነበረውን ተግባራት ገምግመዋል።


አብያተ ክርስቲያናቱ በአገሪቷ እየባሰ የመጣውን ዘረኝነት፣ መከፋፈል፣ በቀልና ጥላቻ ለማስወገድ ተከታታይ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስተያየታቸውን የሰጡ የሃይማኖት አባቶች ገልጸዋል።


በስነ ምግባርም ወጣቱን ማነጽና ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ዜጋ ማፍራት የሚቻልባቸውንም መንገዶች ጠቁመዋል።


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስርቲያን የምስራቅ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ተወካይ አባ ጴጥሮስ፤

የኢትዮጵያ መዕሃፍ ቅዱስ ማህበር ዋና ጻሃፊ አቶ ይልማ ጌታሁን በበኩላቸው አብያተ ክርስቲያናት ከሚሰጡት አስተምህሮና ካላቸው ተከታይና ተቀባይነት አኳያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ገንቢ ሚና መጫወት ይችላሉ  ብለዋል።

በመሆኑም ማህበሩ ቤተክርስቲያኑ ቀደም ሲል ይሰሩ ከነበረው በተሻለ በህዝቦች አንድነትና ሰላም ላይ እንዲሰሩ አቅጣጫ የሚያሳይ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም