የድሬዳዋ አስተዳደር ለህግ የበላይነት መከበር ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ተጠየቀ

243

ድሬደዋግንቦት 9 / 2011 የድሬዳዋ አስተዳደር ለህግ የበላይነት መከበር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ።

አስተዳደሩ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እያደረግኩኝ ነው ብሏል።

የምክር ቤቱ የህግ ፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዑመር ሀሰን እንደገለጹት አስተዳደሩ ህገ-ወጥ የሰዎችና የመሳሪያ ዝውውርን በተቀናጀ መንገድ በመከላከል የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ አለበት፡፡

አልፎ አልፎ በአጎራባች ቀበሌዎች የሚነሱ ግጭቶችን አስቀድሞ በመከላከል ሰላምና ጸጥታን እንዲያስከብርም አሳስበዋል።

የአስተዳደሩን ፖሊስ ኮሚሽን አሰራርና አደረጃጀት በማጠናከር የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል እንደሚገባ አመልክተዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ ኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ለድርድር እንደማይቀርብ ጠቁመዋል።

በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር ግጭትን የብሔርና ሃይማኖት ግጭት ለማስመሰል የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው ተናግረዋል። 

ኅብረተሰቡ መረጃንና አጥፊዎችን ከመደበቅ ይልቅ ለጸጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ ኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑን ጠቁመዋል።

በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር ግጭትን የብሔርና ሃይማኖት ግጭት ለማስመሰል የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ መረጃንና አጥፊዎችን ከመደበቅ ይልቅ ለጸጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ሊያግዝ እንደሚገባ ገልጸዋል። 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ማሃዲ ጊሬ በበኩላቸው በአስተዳደሩ ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከከፍተኛ አመራር እስከ ታችኛው እርከን በሚገኘው አመራር ላይ መሰረታዊ ለውጥ ተደርጎ የተቀናጀ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ለ800 የፖሊስ አባላት በጅግጅጋ ከተማ  ስልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

በአስተዳደሩ ለውጥ ለማምጣት ልማትና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።