ደደቢት በሜዳው ባህርዳር ከነማን 5 ለ 2 አሸነፈ

227

ግንቦት  9/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ25ኛ ሳምንት በትግራይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ደደቢት ባህርዳር ከነማን 5ለ2 አሸነፈ።

ደደቢት ባህርዳር ከተማ ዛሬ ያሸነፈው ተመልካች በሌለው ዝግ ስተዲየም ነው።

ዛሬ ባገኘው ውጤት ደደቢት ቀደም ሲል የነበረውን 10 ነጥብ ወደ 13 ማሳደግ ችሏል።

በደደቢትና ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለቦች በትግራይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የደደቢት ደጋፊዎች በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት ደደቢት ከገንዘብ በተጨማሪ በዝግ ስታዲየም እንዲጫወት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድርና ስነ ስርአት ኮሚቴ ቅጣት ማስተላለፉ የሚታወስ ነው።

ነገም መቐለ 70 እንደርታ ከሃወሳ ጋር በበዚሁ ስታዲየም እንደሚጫወቱ ከውድድሩ መርሃ-ግብር ማወቅ ተችሏል።