ቦይንግ የማክስ 737 የሶፍት ዌር ማሻሻያ ማጠናቀቁን ገለፀ

53

ግንቦት 9/2011 የቦይንግ ኩባንያ የሶፍት ዌር ማሻሻያውን ያደረገው በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሁለት አስከፊ አደጋዎች በመከሰቱ ነው ሲል ቢቢሲ በድረ ገፁ አስነብቧል።

ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች በሁለት አስከፊ አደጋዎች ምክንያት ከበረራ ወጪ መሆናቸውን ያስነበበው ቢቢሲ ። 

እንደ ቦይንግ ኩባንያ ገለፃ 207 የሚሆኑ ማክስ 737 አውሮፕላኖች የሶፍት ወር ማሻሻያ ተደርጎላቸዋል።

በሶፍተ ዌር ማሻሻያው አብራሪዎች የተለያዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው ከፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ጋር መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ማሻሻያ ተደርጎለታል ሲል ቢቢስ በመረጃው አስፍሯል።

ቦይንግ ያደረገውን የሶፍትዌር ማሻሻያ የሚያመለክት ማስረጃ ለአሜሪካ የበረራ ቁጥጥር ባለስልጣን ያቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ 8 737 አውሮፕላን ባለፈው መጋቢት ወር ተከስክሶ 157 ሰዎች መሞታቸው ያስታወሰው ዘገባው ከአራት ወር በፊት ንብረትነቱ የኢንዶንዥያው ላዮን አየር መንገድ የሆነው ተመሳሳይ አውሮፕላን ተከስክሶ የ189 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ምክንያት መሆኑንም አልዘነጋም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም