ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በዴንማርክ በሚካሄደው የአፍሪካ-ኖርዲክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብስባ ይሳተፋሉ

74
አዲስ አበባ ግንቦት 29/2010 የአፍሪካ-ኖርዲክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬና ነገ በዴንማርክ ይካሄዳል። በዚሁ ስብስባ ላይ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በየአመቱ የሚካሄው የኖርዲክ-አፍሪካ ስብሰባ የአፍሪካና የኖርዲክ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚገናኙበት መድረክ እንደሆነ ተገልጿል። ለ17ኛ ጊዜ የሚደረገው ይህ ስብሰባ "የጋራ እሴቶች ለጥምር ጎዳናዎች" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት በዴንማርክ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን የመሳሰሉት የኖርዲክ አባል አገሮች ናቸው። ለስራ ጉብኝት ዴንማርክ የሚገኙት ዶክተር ወርቅነህ  ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላርስ ሎኬ ራሙሰን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንደርስ ሳሙየልሰን እንዲሁም ከአገሪቱ ፓርላማ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ጋር በሁለትዮሽ፣ በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም