የኢትዮ- ኬንያ ግኑኝነት ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

229

ግንቦት 7 /2011 ለኢትዮ-ኬንያ ወዳጅነት መጠናከር ዜጎች አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባችዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለው ግኑኝነት በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገለፁ።

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ትናንት በኬንያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በናይሮቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ለወዳጅነቱ መጠናከር ዜጎች አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ በበጐ የለውጥ ጅማሮ ላይ መሆኗን  ተናግረው ሀገርን ለመደገፍ ትንሽ የሚባል እገዛ፣ ትልቅ የሚባል አስተዋፅኦ እንደሌለ ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ ለመስራትና የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ቀደም ብለው ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላት ወዳጅነት የበለጠ እንዲጠናከር ኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸው ይታወሳል።