ዐቃቤ ህግ በአቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ስር በተከሰሱት ላይ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ የክስ ዝርዝር አሰምቷል

102

ሚያዝያ 30/ 2011 ዐቃቤ ህጉ በአቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ስር በተከሰሱና እስካሁን ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች በፌዴራል ፖሊስ በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸውም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ከ6ኛ እስከ 34ኛ ያለውን የክስ ዝርዝር አሰምቷል።

ዐቃቤ ህጉ በአቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ስር በተከሰሱና እስካሁን ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች በፌዴራል ፖሊስ በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸውም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥም ጠይቋል።

ከ1ኛው ተጠርጣሪ ተከሳሽ ክስ በስተቀር በችሎቱ እጃቸው ያልተያዘውና በ9ኛ፣ 11ኛ፣ እና 12ኛው ተራ ቁጥር ስር ላሉት ተከሳሾች  የክስ ዝርዝር አልተደመጠም።

ፍርድ ቤቱ ቀሪውንና ከ35ኛ እስካ 46ኛ ያለውን የክስ ዝርዝር ለመስማትና ለዐቃቤ ህግ የመጥሪያ ትዕዛዝ ጥያቄ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ግንቦት 1 ቀን 2011ዓ.ም ቀጥሯል።

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በ26 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ላይ ክስ የተመሰረተው ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል የወንጀል ምርመራ ሲካሔድባቸው ከጠቀየ በኋላ መሆኑ ይታወሳል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም