በጅማ ዞን የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አብሮነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገቡ

284


ጅማ ሚያዝያ 29 /2011 በጅማ ዞን የሚገኙ ብሔር/ብሔረሰቦች ተወካዮች በሰላም አብሮ የመኖር ባህልን ለማጠናከር ቃል ገቡ።

ነዋሪዎቹ በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ “አብሮነታችን ለሰላማችን! “ በሚል መርህ ውይይት አካሄደዋል።

ከማና ወረዳ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት አቶ ከድር ሁሴን በዞኑ ብሔርን መሰረት በማድረግ ጥላቻና ግጭት የሚታይበትን ሁኔታ ለመቀየር የአብሮነት ባህላችንን ማጠናከር ይገባናል ብለዋል።

ከሊሙ ኮሳ ወረዳ የተሳተፉት አቶ አበባው ወዳጆ መንግሥት ብሔርን በመለየት ልዩነት በሚፈጥሩና ጉዳት በሚያደርሱት ላይ  የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልከሪም ሙሉ  በበኩላቸው በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ለክልሉ ድምቀት ናቸው ብለዋል።

ብሔር/ ብሔረሰብች በአንድ ክልል ሆነ በሀገር ውስጥ መኖራቸው ጥቅም እንጂ፤ ጉዳት የለውምያሉት ከንቲባው፣ይህም ጠቃሚ ባህልና ልምድ የመለዋወጥን እድል ጎላ ያደርገዋል ብለዋል።

በዞን አብሮ በሰላም መኖርን ጥርጣሬና ስጋት ለመክተት የሚጥሩ አካላትን ችላ እንደማይባሉም ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል የአብሮነትና የወንድማማችነት ኮንፍረንስ ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው።