መቀሌ ሰባ እንደርታ ስሁል ሽሬን አሸነፈ

308

ሚያዝያ 27/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የ23ኛው ሳምንት ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ መቀሌ ሰባ እንደርታ ስሁል ሽሬን ሶሰት ለአንድ አሸንፏል።

መቀሌ ሰባ እንደርታ የሊጉን መሪነት ወደ 48 ነጥብ በማድረስ አጠናክሯል።

ያሬድ ከበደ በሶስተኛው፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል በ19ኛውና ናሆል ዮሴፍ በ90ኛው ደቂቃ ያስቆጠሯቸው ግቦች መቀሌ ሰባ እንደርታን ለአሸናፊ አብቅተውታል።

ስሁል ሸሬ በቢስማክ ማኪያ አማካኝነት በ30ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ስሁል ሸሬ19 ነጥብ በመያዝ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በመቀሌ አለም አቀፍ ስታዲዬም የተካሄደውን ጨዋታ 70 ሺህ ያህል ተመልካቾች ተመልክተውታል።